የረጅም ልቦለድ መከፋፈያ መስፈርቶች
ለረጅም
ልቦለድ አይነቶች ወጥ የሆነ የመከፋፈያ መስፈርት አለ ለማለት ቢያስቸግርም አብዛኛዉን ጊዜ ረጅም ልቦለድን
ለመከፋፈል ይዘትን ወይም ጭብጥንና በልቦለዱ ዉስጥ የሚቀርቡ ክንዋኔዎችን መሰረት በማድረግ መከፋፈል የተለመደ
ተግባር ነዉ። ከዚህም በተጨማሪ የተቀረጹ መቼቶችና ገጸባህሪያት ለልቦለድ መከፋፈያ መስፈርት በመሆን ያገለግላሉ።
ይዘትን
ወይም ጭብጥን መሰረት በማድረግ ፖለቲካዊ፣ ስነ ምግባራዊ፣ ስነ ሰባዊ ወዘተ በማለት መከፋፈል ይቻላል። ፖለቲካዊ
ርዕሰ ጉዳዮችን የሚያካትተዉን ፖለቲካዊ፣ ስለ ስነምግባር የሚሰብከዉን ስነ ምግባራዊ፣ የማህበረሰቡን ባህላዊና
ማህበራዊ እዉነታዎች የሚያንጸባርቀዉን ስነ ሰባዊ ልቦለድ በማለት መፈረጅ ወይም መመደብ ይቻላል።
የሚቀረጹ
ገጸባህሪያትን መሰረት በማድረግ ደግሞ አሊጎሪያዊ፣ ታሪካዊ፣ ደብዳቤያዊ ወዘተ በማለት መከፋፈል ይቻላል።
የተቀረጹት ገጸባህሪያት እንስሳትና ረቂቅ ነገሮች ወይም ግኡዛን አካላት ከሆኑ አሊጎሪያዊ፣ ታዋቂ ባለታሪኮች
ገጸባህሪ፥ ታሪካዊ ቦታወች መቼቶች ሆነዉ የሚቀርቡበትን ደግሞ ታሪካዊ ልቦለድ በማለት መመደብ ይቻላል።
ይሁን
እንጂ ከላይ የቀረቡት የመከፋፈያ መስፈርቶች ወጥነት ያላቸዉ ናቸዉ ለማለት አያስደፍርም። ይኸዉም በአንዱ ልቦለድ
ዉስጥ የተገለጹ ጉዳዮች በሌላዉ ዉስጥ ሊገኙ የሚችሉ መሆናቸዉ ነዉ። ለምሳሌ በአሊጎሪያዊ ልቦለድ በገጸባህሪያት
አማካኝነት ፖለቲካዊ ሁኔታዎች ሊተቹ፣ ሊገመገሙና ሊፈተሹ፣ ስነ ምግባር ሊሰበክና አጠቃላይ ስነ ሰባዊ ጉዳዮች
ሊገለጹ ይችላሉ። ይህ የአንዱ ልቦለድ ይዘት በሌላዉ ዉስጥ ተካቶ መገኘት የመከፋፈያ መስፈርቱን የተጣራ አለመሆን
ያሳያል። ከዚህ በመነሳትም የመከፋፈያ መስፈርቱ ክፍተት ያለበት ነዉ ለማለት ይቻላል። ይሁንና የተለያዩ ጥናቶች
ተጠንተዉ የተጣራ መክፈያ እስከሚገኝ በዚህ መስፈርት መጠቀም ይቻላል።
የረጅም ልቦለድ አይነቶች
የልቦለድ
መከፋፈያ መስፈርቶች እነዚህ ናቸዉ ብሎ በርግጠኝነት መናገር እንደሚያስቸግር ሁሉ የልቦለድ አይነቶችንም ይህን
ያህል ናችዉ ብሎ ለመወሰን ያዳግታል። በርካታ የረጅም ልቦለድ አይነቶች እንዳሉ ብርሐኑ (2009፣ 32) ይገልጻሉ።
ከላይ
በቀረበዉ የረጅም ልቦለድ መከፋፈያ መስፈርት መሰረትም የተለያዩ የረጅም ልቦለድ አይነቶች አሉ። እነሱም ፖለቲካዊ፣
ስነ ሰባዊ፣ ስነ ምግባራዊ፣ ደብዳቤያዊ፣ ታሪካዊ፣ አሊጎሪያዊ፣ ምጸታዊ ወዘተ ናቸዉ። ይሁንና የኛ የትኩረት
አቅጣጫ ሶስቱን የልቦለድ አይነቶች ማብራራት ወይም መግለጽ በመሆኑ እንደሚከተለዉ ለመግለጽ ተሞክሯል።
ስነ ምግባራዊ ልቦለድ
ይህ
የልቦለድ አይነት ከህብረተሰቡ እዉነታ ጋር የተቀራረበ ነዉ። ማለትም በታሪኩ ዉስጥ የሚጠቀሱ ቦታዎችና ስሞች ታሪኩ
ከተቀረጸበት ማህበረሰብ ባህል ወግና ልማድ ጋር የተቀራረቡ ናቸዉ። ስነ ሰባዊ ልቦለድ የተቀረጸበትን መቼት (ጊዜና
ቦታ) ከማህበረሰቡ ወግና ልማድ ጋር አዋህዶና እዉነታዊነትን አላብሶ የማቅረብ አቅም አለዉ። ይህ ልቦለድ ሰወች
በተወሰነ ቦታና ጊዜ የፈጸሟቸዉን፣ ወደፊት የሚፈጽሟቸዉንና እየፈጸሟቸዉ ያሉትን ድርጊቶች ከማህበረሰቡ እዉነታ ጋር
በማቀራረብ በገጸባህሪያት አማካኝነት ይገልጻል።
ፖለቲካዊ ልቦለድ
ይህ
የልቦለድ አይነት በመተግበር ላይ ያሉ ፖሊሲዎችን፣ የፖለቲካ ሰዎችን፣ የተለያዩ የፖለቲካ ድሪጅቶችን፣የአስተዳደር
አካላትን ወዘተ በገጸባህሪያት አማካኝነት በመሳል ስላለዉ ፖለቲካዊ ሁኔታ የሚገልጽ የልቦለድ አይነት ነዉ። ይህ
የልቦለድ አይነት ያለፈዉ ፖለቲካዊ ስርአት ምን እንደነበር፣ የዛሬዉ ምን እንደሚመስል አዝናኝና እዉናዊ በሆነ መልኩ
ይተችበታል።
ፖለቲካዊ
ልቦለድ የደራሲዉ የግል ስሜት የሚንጸባረቅበት ሳይሆን ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸዉን ሀሳቦች የሚያቀርብ፣ በቀጥታ ስለ
ፖለቲካዊ ክስተቶች የሚገልጽ፣ የሚተረጉምና የሚተነትን ዝርዉ የፈጠራ ስራ ነዉ ሲሉ ሞሪስ ጆሴፍን ጠቅሰዉ ይገልጻሉ።
በፖለቲካዊ ልቦለድ ዉስጥ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸዉ ሀሳቦች ወሳኝነት አላቸዉ። መቼቱም አንድ ፖለቲካ የነበረበት ጊዜና ቦታዎች ናቸዉ ሲሉ ኤርቪንግ ይገልጻሉ።
ከእነዚህ ሁለት ምሁራን ሃሳብ የምንረዳዉ ፖለቲካዊ ልቦለድ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸዉን ሃሳቦች የሚገልጽ የደራሲዉ የምናብ ዉጤት መሆኑን ነዉ።
ሰዋሰዉ
ምላሽ ይስጡሰርዝ